BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 4 February 2014

የገዥውን ፓርቲ የፈረጠመ ጡንቻ “ቼክ” የሚያደርግ ሚዛ ናዊ ሀይል እስካልተፈጠረ ድረስ ኢህአዴግ እንዲህ እየቀለደ መቀጠሉ አይቀርም።


50 ዓመት
ባለፈው ሳምንት በአረና ለትግራይ፣ አሁን ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ አፈናና ድብደባ ተፈጽሟል። በፓርቲዎቹ አመራሮች ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው እና እየተፈፀመ ያለው በሌላ አንዳች ምክንያት ሳይሆን ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን ለመተግበር በመሞከራቸው ነው። አረናዎች በአዲግራት ህዝባዊ ስብሰባ ፤ሰማያዊዎች ደግሞ በጎንደር የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ መነሳታቸው ነው በድንጋይ ያስወገራቸው፣ በዱላ ያስደበደባቸው፣ ያሣሰራቸው፣ ንብረታቸውን ያስነጠቃቸው እና በታጣቂዎች ያስከበባቸው። ይህ የሚያስተላልፍልን ግልጽ መልዕክት፦ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ተመዝግባችሁ ከመቀመጥ ውጪ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አትችሉም”የሚለውን የኢህአዴግን አቋም ነው።.....................

አዎ!ቀደም ሲል በሀገራቸው ላይ የውጪ መንግስታትን ድርጊት(በግራዚያኒን ሐውልት የጣሊያንን፣ በስደተኞች ጉዳይ የሳዑዲን መንግስት ) ለመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው በቆመጥ የተደበደቡ ፓርቲዎች፣አሁንም ስብሰባና ሰልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ ተመሣሳይ የግፍ ጽዋ እየተጎነጩ ነው።
አቶ መለስ የዛ ሬ አምስት ዓመት አካባቢ ሓዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ ሰባተኛ ጉባዔ ላይ፤ በሊቀመንበርነት የሚመሩት ኢህአዴግ እቅዱን ለማሳካት ቢያንስ እስከ 50 ዓመት በስልጣን ላይ ለመቆዬት ማቀዱን ተናገሩ። አቶ መለስ ዛሬ የሉም። የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ዛሬ ከአምስት ዓመት በሁዋላ ያንኑ የአቶ መለስን ቃል ደግመውታል። “ኢህአዴግ የልማት እቅዱን ለማሳካት ከ40 እስከ 40 ዓመት ስልጣን ላይ መቆዬት አለበት” ነው ያሉት አቶ በረከት- ለኢሳት የደረሰውና በዜና ይፋ የሆነው የድምጽ መረጃ እንደሚያረጋግጠው።
እንግዲህ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትግል ገና በስልጣን ላይ 50 ዓመት ለመቆዬት ከወሰነ ፓርቲ ጋር ነው። ትግሉ እጅግ ከባድና ረዥም ይመስላል።
… እናም ከእንደዚህ ዓይነት አፈናው ከጠነከረ ሥርዓት ጋር የሚደረግ ትግል ከፍተኛ ጽናትን፣ ድፍረትን፣ ትዕግስትንና ብልህነትን ይጠይቃል። ከሁሉም በላይ ቢያንስ ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በፓርቲዎች መካከል መተባበር ያስፈልጋል።የገዥውን ፓርቲ የፈረጠመ ጡንቻ “ቼክ” የሚያደርግ ሚዛ ናዊ ሀይል እስካልተፈጠረ ድረስ ኢህአዴግ እንዲህ እየቀለደ መቀጠሉ አይቀርም። ሚዛናዊ ሀይል ሊፈጠር የሚችለው ደግሞ በየቦታው የተበጣጠሰው የህዝብ ድምጽ ወደ አንድ መምጣት ሲችል ነው። ትግሉ በጠመንጃ እና በህዝብ መካከል የሚካሄድ እንደሆነ የሚያምኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉ- ጠመንጃ ሊሸነፍ የሚችለው ህዝቡ በአንድ አገራዊ አቋምና አስተሣሰብ ላይ መቆም ሲችል እንደሆነ በማጤን፤ ይህ እንዲሆን የሚችሉትን ሁሉ ሊያደርጉ እና ያሉትን አማራጮች ሁሉ አሟጠው ሊጠቀሙ ይገባል።
ያ ሲሆን ነው 50 ዓመት ነክሶ ለመያዝ ያቀደው ጥርስ ሲሆን ሲሆን በ50 ቀን፤ ሳይሆን በ 5 ዓመት ሊወልቅ የሚችለው።
ያ ሲሆን ነው፦
“ ይወላልቃሉ፣
ጥርሶችሽ በሙሉ።
ጆሮሽን ክፈቺው፣ ልንገርሽ ስሚ-እሙ፣
ነክሶ የያዘ ጥርስ፣ አይቀርም መድከሙ።” እያሉ በተስፋ ማንጎራጎር የሚቻለው።
“እባብ የት ነው የምትሄደው?”
“መተማ”
“ልብማ”
ወይ የልብ ሃሳብ!!

No comments:

Post a Comment