BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 14 February 2014

በዓለም ላይ ትልቁና ከባዱ እንዲሁም ጥበብ የሚጠይቀው ስራ ሀገር ማስተዳደር ነው፡፡

ከሳሙኤል ተወልደ በርሄ( ኖርዌይ ሃሽታ)

    የብዙ ሚሊዮኖች መውጫ መግቢያ መኖሪያ ማደሪያ የሆነች ሃገርን ለማስተዳደር የመሪነት የሚመጥንተሰጥኦ   ይገባዋል:: በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ የመሪነት ጸጋ (ተሰጥኦ) ሳኖራቸው ሃገር እንተዳድሩ የሚመረጡ ግለሰቦች ማየት የተለመደ የፖለቲካ ክስተት ነው:: ይህ ክስተት ይበልጡን የሚስተዋለው ኢህአዴግ መንግስት በሙት መንፈስ በደከመ (በረጀእንዲሁም በህመም በሚሰቃይ ሰው ማስተዳደር ከጀመረ ሰነባብቷል:: በዓለም ላይ ሃገርን እንደቀላል (ተራ ነገር) የሩ መሪዎች ክምችት ነች: አፍሪካዬ! ከአፍሪካም ኢትዮጵያ ነች ብል ታሪክ እና ትውልድ ይወቅሰኛል ብዬ አላስብም:: ይልቁንም ኢትዮጵያ በጥቂት ቁምነገረኛና  በበርካታ ቀልደልደኛ “መሪዎች የተዘወረች ሃገር መሆንዋን ያለፈው ሆነ የዛሬው ታሪካችን ህያው ምስክር ይሆነኛል:: ያለፉት ሥርዓቶች (ለጊዜው) የዛሬውን መንግስት የኢህአዴግን ክልላዊና ሃገራዊ አስተዳደር ማቃኘት ወደድኩ::በተባረከና በተማረ መሪ መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል አርበ ሰፊ መሆኑ አያከራክርም:: መባረክ ከላይ (ከሰማይመማርም (ከምድር)ነ:: የሃገራችን ክልላዊና ሃገራዊ አስተዳዳሪዎች በሁለትና በሶስት ዲግሪ የተከበቡ መሆናቸው እንጂ የተባረኩ ይሁኑ አይሁኑ ማወቅ አይቻልም:: በርግጥ የሚያሳየው የሥራ ፍሬ በመነሳት የተባረከ መሆን አለመሆኑን ከፍ ሲልም ማወቅ የሚቻል ይመስለኛል:: ኢት በማን ነው እየተመራች ያለችው? ለምናነሳው ጥያቄ የተባረከ መሪ ነው የሚል መልስ መስጠት አዳጋች ነው የመለስ ራዕይ” የምትለዋ ቃል ኢትዮጵያ መንበሩ ላይ በሌለ መሪ (በሙት መንፈስእንደምትመራ  መሆንዋን ማረጋገጫ የሚሆን ይመስለኛል:: በህይወት ያሉት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ምንም እንኳን ሃገሪቱን በራሳቸው አቅጣጫ የመዘወር አዝማሚያ ቢኖራቸውም በህይወት የሌሉትን የአቶ መለስ መንፈስ ራዕይ ስም በሃገሪቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ እያሳረፈ ያለው ተፅዕኖ ቀለል የሚባል አይደለም:: 
በዚህ ምክንያት በህይወት በሌለ ሰው (መንፈስ) የምትመራ መሆንዋን መመስከር ይቻላል:: ዓይኑ ለማየት አቅሙ የደከመ አጋዥ ካልተደገፈው በቀር ከተቀመጠበት የማይነሳ ከእድሜው መግፋት የተነሳ መጦር እንጂ መምራት የማይገባው ሰው በኢህአዴግ እንደነበረ የቅርብ ግዜ ትዝታችን በነበሩት የ100 አለቃ ግርማ ወልጊስ እንደምሳሌ ማስቀመጥ ይቻላል:: እንደ አብዛኞቻችን እምነት አንድ ባለልጣን ለሃገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ተመልካቾች እይታ በሰፊው የተጋለጠ የሃገር ፕሬዝደንት እንደ 100 አለቃ ግርማ እድሜው የገፋ መሆን አልነበረበትም:: የአቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ እድሜ የአካል ብቃት ፈጥኖ የመናገር እና የመንቀሳቀስ ሁኔታ የአንዲት ሃገር ሲምቦል (ምልክት) ወይም ፕሬዝደንት ለመሆን ይፈቀድላቸዋል ብዬ አላምንም ነበር:: ምንም እንኳን የስልጣን ዘመናቸው ቢያከትምም  በርግጥ 100 አለቃ ግርማ በፕሬዝደትነታቸው ኢትዮጵያን መርተዋል ብዬ ባላምንም የእርሳቸው የፕሬዝደትነታቸው ስራ አገር መምራት ሳይሆን ተፅዕኖ አልባ መሆኑን ባምንም ቦታው ቀልጠፍጠፍ ያለ ሰው የሚሻ እንደነበር የሚካድ አልነበረም:: ከዚህ አንፃር አቶ ግርማ ስልጣናቸውን መነጠቅ ከነበረባቸው ጊዜ በላይ መቆየታቸው ሃገሪቱ ጡረታ ሊወጣ በተቃረበ ሰው ተወክላ እንደነበር ያመለክታል:: በቀበሌ በወረዳ በዞን በክልል አስተዳደርና አስተዳዳሪዎች የስራ ውጤት ነው የአንዲት ሃገር እድገትም ሆነ ውድቀት የሚለካው:: ከዚህ ፅንሰ ሃሳብ በመነሳት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ብሄር (ፕሬዝደንት) የሆኑትን አቶ አለማየሁ አቶምሳነ የሥራ ዘመን መገምገም ይቻላል::  አለማየሁ አቶምሳ የክልሉ አስተዳዳሪ ከሆኑበት ግዜ አንስቶ እስካሁን ያለውን ያለውን የሥራ ዘመናቸውን ብንመረምር ከሰሩበት ግዜ የታመሙበት ግዜ ሚዛን እንደሚደፋ እንረዳለን:: ፕሬዝደንቱ በተደጋጋሚ እየታመሙ ከስራ መራቃቸውን ተከትሎ ብዙውን ጊዜ እርሳቸውን እየወከሉ ክልሉን የተመለከት አስተያየትና መግለጫ የሚሰጡት የእርሳቸው ምክትል የሆኑት አቶ አብዱራህማን ናቸው:: አንድ ክልል ያውም ሰፊ የቆዳ ስፋት ያለው የኦሚያ ክልል በፕሬዝደትነት ለማገልገል በርካታ መስፈርቶች ሊኖሩ ያስፈልጋል:: ከመቹ አንዱ ደግሞ የጤና ጉዳይ ነው:: በርግጥ ወዶና ፈቅዶ የሚታመም ባይኖርም የጤና ሁኔታው የፕሬዝደትነት ስራውን ክፉኛ የሚፈታተንበት ሰው ለከፍተኛ ሃላፊነት መሾም በክልሉ ላይ መቀለድ ይመስለኛል:: በም ሆነ በሌላ ምክንያት ከስራ መቅረት ወይም ስራን መበደል በክልሉ አመታዊ ውጤት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እንደማይሆን የተወቀ ነው:: እንግዲህ ከላይ የጠቃቀስኳቸውን ነጥቦች በማገናዘብ ኢትዮጵያ በምን አይነት ሰዎች( አስተዳዳሪዎች) ውጤት መሆንዋን መገንዘብ ይቻላል:: የሞተ ሰው (መለስ)እድሜው ለስልጣን አይመጥን የነበሩት (ግርማ) በጤና እክል ስራውን መስራት ያልቻለ (አለማየሁ)……..ድምር ውጤት ነች:: ኢትዮጵያ! የታደለ ሃገር ህዝብ የተማረ ብሎም የተባረከ መሪ ሲያገኝ እኛ ደግሞ…………….
ቸር ይግጠመን

No comments:

Post a Comment