አበበ ገላው
ታዋቂው ጋዜጠኛ አበበ ገላው በፌስቡክ ገጹ “ተቃዋሚዎች አይተቹም ያለው ማነው?” በሚል ባስተላለፈው አጭር መልዕክት ተቃዋሚዎች ሲሳሳቱና ሲዳከሙ በመተቸት “በወያኔያዊ ቋንቋ ሂሳቸውን” እንዲውጡ ማድረግ ያስፈልጋል አለ::
“በኢትይዮጵያ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ ምናምን የማምጣት አላማ አለን ብለው አውጀው እያንቀላፉ ምንም ሳይሰሩ፣ ህዝቡን ሳያደራጁ፣ ታግለው ሳያታግሉ መግለጫ ብቻ የሚያወጡ ነጻ አውጪዎችን ከመተቸት መቆጠብ የለበንም።” ያለው አበበ ለዚህም ምክንኒያት ሲያቀርብ “ለነጻነት የሚታገሉ የወያኔ ተቃዋሚዎች መከፋፈልና መዳከም የጎዳው የኢትዮጵያን ህዝብ የጠቀመው ደግሞ አረመኔውን የወያኔ ስርአት ስለሆነ ነው።” ይላል።
አበበ በመጨረሻም መል ዕክቱን ሲያስተላልፍ “ይህን የነቀዘና የበሰበሰ አንባገነናዊ ስርአት ገርስሶ ለመጣል በቅንጅትና በህብረት መታገል ወሳኝ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።”
የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በዚህ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?
እንደጋዜጠኛ ሁሉን ነገር ለሕዝብ ማድረስ ግዴታ መሆኑ ቢታመንም፤
እንደጋዜጠኛ ሁሉን ነገር ለሕዝብ ማድረስ ግዴታ መሆኑ ቢታመንም፤
* እውን ተቃዋሚዎችን በአደባባይ መተቸት፣ ሲያጠፉ ማጋለጥ ትግሉን ይጎዳዋል?
* ተቃዋሚዎችን መተቸት ወያኔን ማስደሰት ነው ወይ?
* ተቃዋሚዎችን መተቸት ወያኔን ማስደሰት ነው ወይ?
አስተያየታችሁን እንጠብቃለን፦
No comments:
Post a Comment