ተማሪዎች ለስርዓቱ ታማኝ ካድሬዎች ሁነው ካገለገሉ ሲመረቁ ምርጥ የተባለ ሥራ እንደሚያገኙ ቃል ይገባላቸዋል። እንደውጤቱም ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ይዘው ለመመረቅ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ታማኝ ካድሬ መሆን ይቀላቸዋል።
ግን በመንግስት መስርያቤት ለመቀጠር የሀገር ዜጋ መሆን በቂ ነው። የሁሉም ሰው መብት ነው። ለማወዳደር ከተፈለገ ደግሞ (የፖለቲካ ታማኝነት ሳይሆን) የትምህርት ማስረጃና ብቃት እንደመስፈርት ሊወሰድ ይችላል።
የመንግስት መስርያቤት በፖለቲካ ኣመለካከት፣ ዝምድና (ባጠቃላይ በሙስና) እየተያዙ ብዙ (በስርዓቱ ደህና ሰው የሌላቸው የዩኒቨርስቲ ሙርቃን) ስራ ኣጥተው እየተንገላቱ ይገኛሉ። ኣብዛኛው የስራ ኣጥነት ሁኔታ በፍትሕ እጦት ምክንያት የተፈጠረ ነው።
ስራ የያዙም ቢሆኑ፡ እድገታቸው (የደመወዝ ጭማሪ ኣክሎ) የሚወሰነው በስራ ገበታቸው ባሳዩት የኣፈፃፀም ብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ኣመለካከታቸው ነው። ይህ ተግባር ፍትሕ ያጎድላል፤ ዜጎችም ይጎዳል። ሲል የገለጸው የመቀሌው ዩኒቨርስቲ መምህር እና የአረና የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባል የሆነው አብርሃ ደስታ ነው ። ይኅንን አያይዞ ሲጠቁምፖለቲካዊ ሙስና በሃገሪቱ ላይ መንሰራፋቱን እና መቆም እንደሚገባው ንጹህ ዜጋዎችን ማፍራት ስንችል ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ ሊያጎበድዱ የሚችሉ ፣ሃገራዊ ግዴታም ሆነ ፍቅር የማኖራቸውን እና ሌሎችን የፖለቲካ አቅጣጫ እንዳያዩ የሚያደርጉ እቅድ ይዞ እንደሚንቀሳቀሱ ጠቁሞአል ። ቀድሞ የሃገር ወይንም የፖለቲካ ለውጥ የሚነሳው ከዩንቨርሲቲዎች በሚነሳ አተካሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ለጥቅም የተገዛ ወጣት ብቻ የሚፈለፈልበት ጉሮኖ ሆኖአል ሲል ጠቁሞአል ።
No comments:
Post a Comment