የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በመሆናችን ብቻ ምክንያት እተፈለገ ስም እየተለጠፈብን እንደበደባለን መሬታችንንም እንቀማለን ሲሉ አማረሩ፡፡ የፓርቲው አባላት 1ኛ. አቶ አዲሱ ተመሰለው 2ኛ. አቶ ካሳዬ አዲሱ 3ኛ. አቶ ተፈሪ ማሞ በኢንስፔክተር ጥላሁን ተቃዋሚ በመሆናችን ብቻ ከፓርቲው እንድንለቅ ድብደባ ማስፈራሪያና በተለያየ ጊዜ እስር እየተፈፀመብን፣ ተጽእኖ እያደረጉብን ነው እንዲሁም መሬታችንን ተቀማን የሚሉ 1ኛ. በፈቃዱ ንጉሴ 2ኛ.ወንድምሲገኝ ይፍሩ 3ኛ. አባቡ ፀጋው ሲሆኑ በአካባቢው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ኃላፊዎችም ማስፈራሪያ ይደርስብናል ከማህበራዊ አገልግሎቶች አግለው ሌሎች እኛን እንዳይከተሉን መቀጣጫ እያደረጉን ነው ከብቶቻችንንም እንዳናሰማራ ተደርገናል፡፡ ይህን ለማጣራት ወደ መንዝ ጌራ ወረዳ ኃላፊዎች ለማጣራት ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም ፤ የወረዳው የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ጥላሁን ጋ ደውለን እኔ ይህን ድርጊት አልፈፀምኩም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment