የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ ቺቦቼ ቀበሌ የእርሻ መሬታቸውን ለአበባ ልማት በሚል እንዲያስረክቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ ከ40 ያላነሱ አርሶአደሮች በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
አርሶደሮቹ በአሁኑ ጊዜ ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የሜጫ ወረዳ በግብርና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአበባ እርሻ እየተባለ በርካታ አርሶአደሮች መሬታቸውን እንዲለቁ እየተደረገ ነው።
No comments:
Post a Comment