የአንድነት ፓርቲ ትላንት የካቲት 23, 2006 ዓ.ም በመሃል ቀጠና ዞን በአዳማ-ናዝሬት የአድዋ በዓልን አከበረ፡፡ በዕለቱ የአንድነት ፓርቲ የአዳማ-ናዝሬት ጽ/ቤትም ለአባላት መተዋወቁን የፓርቲው የአዳማ ከተማ ሰብሳቢ አቶ ምርቱ ጉታ እንዲሁም የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል ፡፡
የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ምርቱ ጉታ እንደገለፀው በከተማው ያሉ አዳዲስና ነባር የአንድነት ፓርቲ አባላት በተገኙበት በተከበረው የአደዋ በዓል ላይ የተለያዩ ግጥሞች የቀረቡ ሲሆን በአድዋ ድል ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ ጨምሮ እንደገለፀው የአድዋ በዓል በትላንትናው ዕለት ከ10 እስከ 12፡30 ሲከበር ታዋቂው አርቲስት አቶ መስፍን ገብሬ እንዲሁም ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ከበዓሉ አከባበር አስቀድሞ ከ8 እስከ 10 ሰዓት በከተማው ያሉ አዳዲስና ነባር የአንድነት ፓርቲ አባላት አዲሱን ቀበሌ 11 ከሃኒ ኬክ ቤት በስተቀኝ ቁጥር 4 ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘውን የፓርቲውን ጽ/ቤት እንዲጎበኙ መደረጉንና በአዳማ በሚደረጉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይትም መደረጉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ አክሎም በየወሩ የውይይት እና የስነጥበብ ዝግጅት ለአዳማ ነዋሪ ለማዘጋጀት መታቀዱንም አስታውቀዋል፡፡
በየወሩ የውይይት እና የስነጥበብ ዝግጅት ለአዳማ ነዋሪ ለማዘጋጀት ታቅዷል
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6378#sthash.LXrwc3tr.dpuf
No comments:
Post a Comment