ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ሽብርተኛ ነህ በሚል መስረት የሌለዉ ክስ ተከሶ የ18 አመት እስራት ፣ በፖለቲካ ዉሳኔ እንደተፈረደበት ይታወቃል። የአሜሪካው የዊጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄን ይቃወማሉ። ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን፣ ለነጻነቱ የጻፈ ሲሉ፣ ከሌሎች አንጋፋ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እኩል አስቀምጠዉታል።
የጆን ኬሪ ይፋዊ ዘለፋ፣ የጋዜጠኛ እስክንደር ሆነ የሌሎች በርካታ ጋዜጠኞችና የሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መታሰር፣ ኢሕአዴግ በአገሩ ካሉ ዜጎቹ ጋር ብቻ ሳይሆን ከበርካታ የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር እንዲጋጭ እያደረገዉ እንዳለ የሚያመላክት ነው።
አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ዋና ደጋፊ እንደሆነች ይታወቃል። በርካታ የአገዛዙ ቱባ ቱባ ባለስልጣናር በአሜሪካ ቤት ያላቸው፣ በአሜሪካ ባንኮች ገንዘብ የሚያሰቀምጡ እንደሆነ ይነገራል። በአመት ከ370 ሚሊዮን ዶር እርዳታም አሜሪካ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ይታወቃል።
በአምባሳደሯ ወይም በስቴት ዲፓርትመንት በአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊ ደረጃ ሳይሆን፣ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደረጃ የነ እስክንደር ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት፣ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጆን ኬሪ፣ በአደባባይ እስክንደርን መጥቀሳቸው፣ ምን ያህል በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከላይ ያሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት እያሳሰበ እንዳለ የሚያሳይ ነው።
ጆን ኬሪ የሚከተለውን ነበር ያሉት፡
“The truth is that some of the greatest accomplishments in expanding the cause of human rights have come not because of legislative decree or judicial fiat, but they came through the awesomely courageous acts of individuals, whether it is Xu Zhiyong fighting the government transparency that he desires to see in China, or Ales Byalyatski, who is demanding justice and transparency and accountability in Belarus, whether it is Angel Yunier Remon Arzuaga, who is rapping for greater political freedom in Cuba, or Eskinder Nega, who is writing for freedom of expression in Ethiopia, every single one of these people are demonstrating a brand of moral courage that we need now more than ever.”
No comments:
Post a Comment