ምናሴ መስፍን በዚህ ሰሞን ከረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ሳነብና ሳዳምጥ ነበር። ካነበብኩት መካከል አንዱ ላይ ድንገት አይኔን አሳረፍኩኝ። በርግጥ በወያኔ ካድሬዎች የተፃፈው ነበር። ረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ የኢትዩጵያን ክብር አዋረደ የሚል አስተያየት። ግን ኢትዮጵያ የተዋረደችው እውን በኀይለመድህን ወይስ እራሱ ወያኔ መንግስት ነኝ ብሎ አገራችንን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው???
ህውሀት በአገራች ላይ የማይቆጠር በደልና ውርደት የፈፀመ አምባገነን መንግስት ለመሆኑ የማይረሳ ቢሆንም የቅርብ ጊዜውን በኢትዩጵያዊያን ህሊና ከማይረሳው ክፉ ትዝታዎች መካከል እስቲ ጥቂቶቹን ላስታውሳቸው። መቼም እነርሱ አድርገውና አጥፍተው እንዳልተደረገ ሆነው መቅረብ ጠባያቸው ነው “ ታሪክ ይቅር የማይለው ውርደት” ነው ።
ዓለምን ጉድ ያሰኘው በሳውዲ አረብያ ይኖሩ በነበሩ ኢትዮጵያን ላይ የደረሰውን ግፍና ስቃይ የሚረሳ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ታድያ ህገወጥ እስራት፥ድብደባ፥አስገድዶ መድፈርና ዝርፊያ ሲደረግ የት ነበሩ?ይሄ ብቻ አይደለም። በአገር ቤት ያሉ ኢትዩጵያዊያን የወገኖቻቸውንና የልጆቻቸውን የመከራ ብዛት ለመቃወም በወጡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወያኔ መንግስት የወሰደው ግፍ የሳውዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪዎችና ህዝብ ካደረሱባቸው ጥቃት ያልተናነሰ በአገር ውስጥ ባሉት ላይ የፈፀሙት በደል የኢትዩጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በእንባ ሲራጨ በየአደባባዩ ታይቶል። በስደትም ያለው በሰላማዊ ሰልፍ በየኤምባሲዎቹ ቁጣውንና ንዴቱን በመግለጥ ጥቃቱ እንዲቆም ጠይቆል። ህውሀት ግን የሳውዲ አረብ ባላህብቶች በኢትዩጵያ ውስጥ ያላቸውን ኢንቨስትመት ጥቅም በማስቀደም ኢትዬጵያንን ያዋረደ ተግባር የፈፀመ አረመኔ መንግስት ነው። ከዛ በፊት የሆነው ኢትዩጵያውያን የሚወክለው ኤምባሲ ተብዬ በዱባይ በወያኔ ኤምባሲ በር ላይ ወጣት አለም ደቻሳ የድረሱልኝ ጥሪ እየጮህች እያሰማች ሊረዳት ባለመፈለጋቸው የወጣቱአን ህይወት ከሞት መታደግ አልተቻለም። የዜግነት ግዴታ መወጣት በማይችሉ ሆድ አምላኪ አምባሳደር ተብዬዎች የእህታችንን ህይወት አስነጠቁብን። ይህ ክብር ወይስ ውርደት ??? እነሱነታቸውን የሚገልጠው አንድ ነገር ብቻ ነው። " ነውራቸው ክብራቸው” ክብራቸው ነውራቸው ብቻ ነው"
በሌላ በኩል ከሀገር ጥቅምና ክብር ይልቅ ከአባቶቻቸው የወረሱት ባንዳነት ብቅ ብሎ የወያኔ መንግስት የሰራው ስራ የኢትዮጵያን ግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት የሚጻረሩ ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ በምስጢር ከሱዳን መንግሥት ጋር ውል በመፈራረም፤ ርዝመቱ 1,600 ኪ.ሜ ስፋቱ ከ30 እስከ 50 ኪ.ሜ የሚደርሰውን በምዕራብ ኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ለም መሬት አሳልፎ ሰጥቷል። ከትውልድ መንደራቸው የተፈናቀሉ ሕዝባች ብዛት ቁጥር ስፍ የለውም ። ይህም ሆኖ የህዝብን መፈናቀልና መንገላታት ያላሳዘነው የሕዋኃት መንግስት ከህዝብ ችግር ይልቅ ፀረ-ኢትዬጵያዊ ተግባር በማስፉፉት ላይ ይገኛል። ይህውም ሱዳን በወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ትግል ወቅት ላደረገችለት ድጋፍ እንደ እጅ መንሻ ያቀረበው እንደሆን ተደርሶበታል ። ይኸውም ለኛ የሚሰጠን ትርጉም “ከአገር ክብር ይልቅ ውርደት መራጭ ” መሆናቸውነ ነው ። ታዲያ ይህንን የሰራና በመስራት ላይ ያለ ከንቱ ስብስብ ስለ ሀገር ክብር ለማውራት ብቃት እንዴት ይኖረዋል ? በኢትዩጵያ የተንሰራፉት ያለፉት ሥርአቶች በሕዝባቸው ላይ ብዙ በደል ቢፈፅሙም ሕዝባቸውን ለባእዳ አሳልፈው አልሰጡም። የሀገራችንን ዳር ድንበርም አልቆረሱም።
ለመሆኑ ረዳት ካፕቴን ኀይለመድህ አበራ አንድ ትልቅ መልክት ለማስተላለፍ የፈለገ አይመስልም?ነው እንጂ። በጣም የሚገርመው የፓለቲካ ተቃዎሚዋችና አክቲቨስቶች፥የሰባዊ መብት ተከራካሪዎች፥ሲብል ድርጅቶች ለሚጮሁለት ለዚሁ ነገር ነው እኮ እርሱ በተለየ መንገድ ለአለም ህዝብ ያሳየው። የአለም ሚዲያ በአንድነት ያስተጋቡት ይህ በኢትዩጵያ ያለውን መንግስት ጥያቄ ውስጥ የጣለ ጀግና ረዳት መንገደኛው ሳይረብሽ ምቾታቸውን ጠብቆ ያለፍርሀትና ያለሽብር መደናገጥና መርበትበት በሰላም ኣውሮፕላኑን ማሳረፉ ራሱ የተዋጣለት ባለሙያ መሆኑን ያሳያል። የስኬት መለኪያው የተመቻቸ ኑሮ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ነፃነት የሰባዊ መብትን፥ዘረኝነትን መቀበል አለመፍቀድ ጭምር ነው። ሃይለመድህን ድንቅ ነው።ለመሆኑ ማንነው አገራችንን ያዋረደና ያስደፈረው? ካፕቴኑ መይስ ገዥው ህውሀት???
ኢትዬጵያ አገራችን ለዘላለም ትኑር !!!
አመሰግናለሁ
No comments:
Post a Comment