Friday, January 31, 2014
ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።
በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።
የታሪክ ሊቃውንት የነጋሥታቱን ብርቱና ደካማ ጎኖቻቸውን እና የሰሩትን ታሪክና ገድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ፣ ሕዝቡም በተራው ያለፉት ነገሥታት የጣሉበትን የጀግንነት አደራ እንዲጠብቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ ዝና እና ክብር እንዲሁም ታሪክና የታሪክ ቅርሶቿ በክብር እንዲንከባከባቸው በሰጡት አደራ መሰረት ኢትዮጵያ ለማንም ቅኝ ገዢ ሳትንበረከክ በዓለም ደረጃ ዝነኛ ሆና የወጣች ሃገር እንድትሆን አድርገዋታል።...........