ከሳሽ የፌደራል አቃቢህግ አቀራረባቸውን አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ ተቃውሞ ያቀረበ ሲሆን ፥ ማን ለማን እንደሚመሰክር እና ጭብጡን እንዲያቀርቡ ጠይቋል።ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤቱ የአቃቢህግን አቤቱታ በመቀበል ጭብጥ አስይዙ ብሎ ሲበይን ፥ የተከሳሽ ጠበቆች ይህን ለማድረግ የአንድ ወር ጊዜ ጠይቀዋል።ችሎቱ የራሱን የጊዜ ሰሌዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፥ በብይኑ መሰረት መዝገቡን ለመመልከት ለመጋቢት 20 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
No comments:
Post a Comment