BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 8 January 2014

በቦረና ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ 4 ሰዎች ተገደሉ

ኢሳት ዜና:- ባለፈው እሁድ በቦረናና በቡርጂ ማህበረሰብ አባላት መካከል በተነሳው ግጭት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከቡርጂ 3 ከቦረና ደግሞ አንድ ሰው ተገድሎአል። ከ4 ሺ በላይ ነዋሪዎችም ቀያቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል። ጥቂት የፌደራል ፖሊሶች ሜጋ እየተባለች ወደ ምትጠራዋ ከተማ ተንቀሳቅሰዋል። ይሁን እንጅ ግጭቱ ወደ ሚካሄድባቸው ከሜጋ ከተማ ወደ 12 ኪሎሜትሮች ርቀው ከሚገኙት ጎዳቤሮ፣ 

ባታንጋላዶ እና ኦላ ጫፋ ወደ ሚባሉት ቀበሌዎች............

ባለመንቀሳቀሳቸው ግጭቱ እስካሁን መቀጠሉን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የግጭቱ መነሻ አንድ የቦረና ሰው ተገድሎ በመገኘቱ ሲሆን፣ ቦረናዎች ግለሰቡን የገደሉት ቡርጅዎች ናቸው በሚል ጥቃት መሰንዘራቸውንና 3 ሰዎችን መግደላቸውን ይናገራሉ። አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ ቦረናዎች በቡርጂዎች ላይ ጥቃት እንዲሰነዝሩ ቅስቀሳ ያደረጉት የልዩ ዞኑ ምክትል አዛዥ የሆኑት አቶ ሊባን አሬሮ ናቸው። አቶ ሊባን የተባሉት ባለስልጣን በምን ምክንያት እንደሞተ ያልታወቀውን ሰው ቡርጅዎች ገድለውታል ብለው የአካባቢውን ሰው ቀስቅሰው ወደ ግጭት እንዲያመራ አድርገውታል። በባለስልጣናት በኩል ያለውን አስተያየት ለማካተት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

የወረዳው ባለስልጣናት 5 የቡርጅ ብሄረሰብ አባላትን ይዘው ማሰራቸውንና የቦረናን መሬት ለቃችሁ ውጡ ብለው እንደገለጹላቸው ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።

በቡርጅና በቦረናዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መነሻ በቅርቡ ኬንያ ውስጥ በገብራና በቦረናዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ቡርጅዎች ከገብራዎች ጋር ጎን ቆመው ቦረናዎችን ወግተዋል በሚል የመንግስት ባለስልጣናት ቦረናዎችን እንዲነሱ በማድረጋቸው ነው በማለት ገለልተኛ ወገኖች ለኢሳት ገልጸዋል።



No comments:

Post a Comment