BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 7 January 2014

ላለፈ ክረምት ...............

ወደ ላይ ለመውጣት ግዜ፣ ጉልበትና ጥረት ይጠይቃል። ለዚህም ነው ህዝብና ሀገር ወደ ዉህደትና አንድነት ለማምጣት የሚከብደው፤ የሀገር አንድነት ለመጠበቅ ወደ ላይ ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ ግለሰቦች በቁጥር ጥቂት የሚሆኑ። ወደ ታች (ወደ ብሄርና ጎጥ) ለመውረድ ግን ቀላል ነው። ዓይን ጨፍኖ መንሸራተት (መንከባብለል) ብቻ በቂ ነው። 

ለዚህም ነው ብዙ ፖለቲከኞች ወደ ላይ ለመውጣት ከመጣር ቁልቁል ይዘው መውረድ የሚመርጡ። ወደ ላይና ወደ ታች ስንጓዝ ፍጥነታችን በመሬት ስበት ላይ የሚመሰረትን ያህልየአንድነትና የክፍፍል ሓሳቦች ስናራምድም የህዝቦች የፖለቲካ እውቀት ደረጃ እንደ ስበት ሁኖ ያገለግላል። ያለፈው በደል እየቆጠሩ ቁልቁል መውረድ አሁን ላለው በደል መፍትሔ ሊሆን አይችልም። 
ያለፉ ስርዓታት ህዝብን ለመግዛት ሃይል ይጠቀሙ ነበር። ያሁኑ ጉዳያችን ያለፈውን በደል የማይደገምበትና ያሁኑ ጭቆና የሚወገድበት መንገድ ማመቻቸት እንጂ ባለፈው በደል መቆዘም መሆን የለበትም። 'አሁኑኑ ጭቆና እናስወግድ!' በሚል ሐሳብ እስማማለሁ። የኔ ጥያቄ; 'ያለፈውን በደል ማስታወስ አሁን ካለው ጭቆና ለመውጣት ይረዳልን?' ያለፈው በደል መርሳት የሌለብን በደሉ ላለመድገም እንጂ ባለፈው ግፍ አሁን ለመጣላት መሆን የለበትም። 

No comments:

Post a Comment