አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ የአንድነት ፓርቲ አባል፣ ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ እንደተያዙ ለማወቅ ተችሏል። ፖሊሶቹ እንደ ክስ ያቀረቡት ነገር፣ «የፓርቲውን ሰነድ በወረቀትና በኮምፒዩተርህ ውስጥ ተገኝቷል» የሚል እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ አቶ አለማየሁ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው፣ ህጋዊ በሆነ ፓርቲ መሳተፉቸውና ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ምን ዓይነት ወንጀል እንደሆነ ለማጣራት......... ወደ ሌንሳቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ብንደውልም አስተያየት የሚሰጠንን አላገኘንም፡፡
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ማንም ሰው በየትኛው ህጋ ድርጅት ውስጥ መሳተፍና መጀራጀት እንደሚችል፣ የሀሳብ ነፃነት እንዳለው፣ ያንንም ማንፀባረቅ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ እየሆነ ያለውና በአቶ አለማየሁን ለእስር ያበቃው ግን እጅግ ከዚህ ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት በዕስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ እየተከታተልን እናቀርብሎታለን፡፡
No comments:
Post a Comment