በማይጨው ሆስፒታል 1 ዐመት ባልሞላ የስራ-አስኪያጅነት (CEO) ጊዜው ከ14 በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት( አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ) ያደረሰውና በመጨረሻም በከባድ የሀኪሞችና ተበዳዮች ድምፅ ከሆስፒታል ስራ-አስኪያጅነቱ ታግዶ የቆየው አቶ ብርሃኑ ዛሬ መታሰሩ ተሰምቷል፡፡
በገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ የመዳፈር ወይም የመፈታተን ምልክት እስካላሳየ ድረስ ባለስልጣን የሚባል ፍጥረት አገርም ቢሸጥ እንኳ ምንም በማይነካበት ክልል ያሁኑ የአቶ ብርሀኑ መታሰር ሰሞኑን በማሕበራዊ ድረ-ገፆችና በአንዳንድ በሚድያዎች በሰፊው መዘገቡና ወሬው መሰማቱ እንደ ዋና ምክንያት ተመልክተውታል በስልክ ያነጋገርኳቸው ሰራተኞች፡፡
ዛሬ ላይ በተዋለው አጠቃላይ የሰራተኞች ግምገማ የሰራውን ወንጀልና የሐጢአት ቁልልና፣ የሰራተኛው በደልና ብሶት ሲሰማ ውሎ ወደ ማለቅያው አከባቢ ከስራ- አስኪያጅነት አወረዱት፤ ለከሰአቱ ደግሞ እጆቹ የፊጥኝ ታስሮ ወደ እስርቤት ተወርውሯል፡፡
እሳይ፡ እሰይ! እሰይ! ጊዜያዊው የሰራተኛውና የጠቅላላው ህዝብ ጩኸት ለማስቀየስ ታስቦ ቢሆን እንኳ ይህ ኮርማ ህዝብ ሁሉ እያየው እጆቹ የኃሊት ተጠፍሮ ወደ እስርቤት መወርወሩ ከባድ የህሊና ቅጣት ነው( ህሊና የለውም እንጂ
No comments:
Post a Comment