BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 6 January 2014

“ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት”

እስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አዲሱን የአንድነት አመራር “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት” አላቸው • •

2005 . የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን ያገኘውና  እድሜ ልክ እስራት በገዢው መንግስት ተበይኖበት ቃሊቲ የሚገኘውአንዷለም አራጌ ዛሬ ጠዋት ሊጠይቁት የሄዱትን አዳዲሶቹን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገልአንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋአለኝ” ማለቱን ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን እና ካቢኔያቸውን በምርጫ አሰናብቶ በአዲስ የሾመው አንድነት ፓርቲ፤አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ስልጣናቸውን ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ ሥራቸውን ያደረጉት  እስር ቤት የሚገኙትንየፓርቲዎቻቸውን አባላት መጠየቅ ነበር። በዚህም መሠረት አዳዲሱ አመራር እስር ቤት ከሚገኙት የድርጅቱ አመራሮችና አባላትየሚያበረታቱ ምክሮችን መቀበሉን ከዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

አንዷለም አራጌ በአዲሱና በወጣት በተገነባው የአንድነት ፓርቲ አመራር ደስተኛ መሆኑን ገልጾ “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገልአንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋአለኝ” ብሏቸዋል። ይኸው የአንድነት ፓርቲ አመራር እዛው ቃሊቲ የሚገኙትን እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችየሕሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ጠይቆ መከልከሉ የታወቀ ሲሆን ወደ ዘዋይ ያመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን እዛው እስር ቤትየሚገኙትን  የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንንና በዚያ የሚገኙ ሌሎች እስረኞችንመጎብኘታቸውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። 

በሕወሓትኢሕአዴግ አስተዳደር “በሽብርተኝነት ወንጀል” ተከሷል፤ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ደግሞ የሕሊና እስረኛ ነውየሚባለው አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም  እስር ቤት ተቃዋሚዎች የእኔን እስር ቤት መማቀቅ ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም፤ሕዝቡን ለማታገል ልትጠቀሙበት ትችሉ ነበር ሲሉ የነበረውን ድክመት መግለጹን -ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment